መዝሙር 144:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጐተራዎቻችን በተለያየ የእህል ዐይነት፣ የተሞሉ ይሁኑ፤ በጎቻችን እስከ ሺሕ ይውለዱ፤ በመስኮቻችንም እስከ ዐሥር ሺሕ ይባዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕቃ ቤቶቻቸንም ይሞሉ፥ በየዓይነቱም ዕቃ ይኑራቸው፥ በጎቻቸንም ብዙ ይውለዱ፥ በማሰማርያችንም ይብዙ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጐተራዎቻችን በልዩ ልዩ ዐይነት እህል የተሞሉ ይሁኑ፤ በመስኮቻችን ላይ የተሰማሩት በጎች በሺህ የሚቈጠሩ ግልገሎችን እየወለዱ ይብዙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንግሥትህ የዘለዓለም ሁሉ መንግሥት ናት፥ ግዛትህም ለልጅ ልጅ ነው። |
የምትወቁት እህል፣ የወይን ዘለላ እስከምትቈርጡበት ጊዜ፣ የምትቈርጡትም የወይን ዘለላ፣ እህል እስከምትዘሩበት ጊዜ ያደርሷችኋል፤ ምግባችሁን እስክትጠግቡ ትበላላችሁ፤ በምድራችሁም ላይ ያለ ሥጋት ትኖራላችሁ።
በቤቴ መብል እንዲኖር፣ እኔንም በዚህ እንድትፈትኑኝ ዐሥራቱን ሁሉ ወደ ጐተራ አስገቡ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ “የሰማይን መስኮት የማልከፍትላችሁ፣ የተትረፈረፈ በረከትንም ማስቀመጫ እስክታጡ ድረስ የማላፈስስላችሁ ከሆነ ተመልከቱ።
ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው በእያንዳንዱ ቃል እንጂ፣ በእንጀራ ብቻ እንደማይኖር ሊያስተምርህ አስራበህ፤ አንተም ሆንህ አባቶችህ የማታውቁትን መና መገበህ፤