ጠላቶቻችን ሁሉ ይህን ሲሰሙ፣ በዙሪያችን ያሉ አሕዛብ ሁሉ ፈሩ፤ በራሳቸው መተማመንም አልቻሉም፤ ምክንያቱም ይህ ሥራ የተከናወነው በአምላካችን ርዳታ መሆኑን ተገንዝበዋል።
መዝሙር 129:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ፣ ዐፍረው ወደ ኋላቸው ይመለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጽዮንን የሚጠላ ሁሉ ይሸነፍ! ወደ ኋላውም ይመለስ! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ስለ ስምህ ተስፋ አደረግሁህ፤ ነፍሴ በሕግህ ታገሠች። |
ጠላቶቻችን ሁሉ ይህን ሲሰሙ፣ በዙሪያችን ያሉ አሕዛብ ሁሉ ፈሩ፤ በራሳቸው መተማመንም አልቻሉም፤ ምክንያቱም ይህ ሥራ የተከናወነው በአምላካችን ርዳታ መሆኑን ተገንዝበዋል።
ሐማም የደረሰበትን ሁሉ ለሚስቱ ለዞሳራና ለወዳጆቹ ሁሉ ነገራቸው። አማካሪዎቹና ሚስቱ ዞሳራም፣ “በፊቱ መውደቅ የጀመርህለት መርዶክዮስ ዘሩ ከአይሁድ ወገን ከሆነ፣ ልትቋቋመው አትችልም፤ ያለ ጥርጥር ትጠፋለህ” አሉት።
ጌታ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ የሚያደርገውን ሁሉ ከፈጸመ በኋላ፣ እንዲህ ይላል፤ “የአሦርን ንጉሥ ስለ ልቡ ትዕቢትና ስለ ንቀት አመለካከቱ እቀጣዋለሁ፤
የተራበ ሰው በሕልሙ ሲበላ ዐድሮ፣ ነገር ግን ሲነቃ ራቡ እንዳልለቀቀው፣ የጠማውም ሰው በሕልሙ ሲጠጣ ዐድሮ፣ ነገር ግን ሲነቃ እንደ ዛለና ጥማቱም እንዳልተወው፣ የጽዮንን ተራራ የሚወጋ፣ የአሕዛብ መንጋ ሁሉ እንዲሁ ይሆናል።
እግዚአብሔር በርሱ ላይ የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ “ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ፣ ንቃሃለች፣ ታቃልልሃለችም፤ የኢየሩሳሌም ልጅ፣ አንተ ስትሸሽ ራሷን ነቅንቃብሃለች።
የምድር አሕዛብ ሁሉ በርሷ ላይ በሚሰበሰቡበት በዚያ ቀን፣ ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ የማይነቃነቅ ዐለት አደርጋታለሁ፤ ለማነቃነቅ የሚሞክሩ ሁሉ ራሳቸውን ይጐዳሉ።
“በዚያ ቀን የይሁዳን መሪዎች በዕንጨት ክምር ውስጥ እንዳለ የእሳት ምድጃ፣ በነዶም መካከል እንዳለ የፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፤ በግራና በቀኝ ዙሪያውን ያሉትን ሕዝቦች ይበላሉ፤ ኢየሩሳሌም ግን ከስፍራዋ ንቅንቅ አትልም።