ስለዚህም ያዕቆብ ለቤቱ ሰዎችና ዐብረውት ለነበሩት ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “በእናንተ ዘንድ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ሰውነታችሁን አንጹ፤ ልብሳችሁንም ለውጡ።
መዝሙር 116:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልመናዬን ድምፅ ሰምቷልና፣ እግዚአብሔርን ወደድሁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሃሌ ሉያ! ጌታ የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና ወደድሁት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጩኸቴንና ልመናዬን ስለ ሰማ እግዚአብሔርን እወደዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብ ሁላችሁ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑት፥ ወገኖችም ሁሉ ያመስግኑት፤ |
ስለዚህም ያዕቆብ ለቤቱ ሰዎችና ዐብረውት ለነበሩት ሁሉ እንዲህ አላቸው፤ “በእናንተ ዘንድ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ሰውነታችሁን አንጹ፤ ልብሳችሁንም ለውጡ።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “በፊቴ ያቀረብኸውን ጸሎትና ልመና ሰምቻለሁ፤ ይህን የሠራኸውንም ቤተ መቅደስ፣ ስሜ ለዘላለም በዚያ ይኖር ዘንድ ቀድሼዋለሁ፤ ዐይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።
እግዚአብሔርም የእስራኤልን ልመና ሰምቶ ከነዓናውያንን በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ሰዎቹንና ከተሞቻቸውን ፈጽመው ደመሰሱ፤ ከዚህ የተነሣም ስፍራው ሖርማ ተባለ።
እርሱን በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም አእምሮህ፣ በፍጹም ነፍስህ፣ በፍጹም ኀይልህ መውደድ፣ እንዲሁም ባልንጀራህን እንደ ራስህ መውደድ ከሚቃጠል መሥዋዕት ሁሉና ከሌሎችም መሥዋዕቶች ይበልጣል።”
ሦስተኛም ጊዜ፣ “የዮና ልጅ፣ ስምዖን ሆይ፤ ትወድደኛለህን?” አለው። ጴጥሮስም ሦስተኛ ጊዜ ኢየሱስ፣ “ትወድደኛለህን?” ብሎ ስለ ጠየቀው ዐዝኖ፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንደምወድድህም ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፤ “በጎቼን መግብ።
ሐናም ዔሊን እንዲህ አለችው፤ “ጌታዬ ሆይ፤ በነፍስህ እምላለሁ፤ እዚህ ቦታ ላይ በአጠገብህ ቆማ ወደ እግዚአብሔር ስትጸልይ የነበረች ያች ሴት እኔ ነኝ።