ይህ ዕዝራ ከባቢሎን መጣ፤ እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ሕግ በሚገባ የሚያውቅ የሕግ መምህር ነበር። የአምላኩ የእግዚአብሔር እጅ በርሱ ላይ ስለ ነበረች፣ የጠየቀውን ሁሉ ንጉሡ ፈቀደለት።
መዝሙር 109:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ እጅህ ይህን እንዳደረገች፣ አንተም ይህን እንደ ፈጸምህ ይወቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ እጅህ ይህች መሆኗን፥ አንተም ይህንን እንዳደረግህ ይወቁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምታድነኝ አንተ ብቻ እንደ ሆንክ ጠላቶቼ እንዲያውቁ አድርግ። |
ይህ ዕዝራ ከባቢሎን መጣ፤ እርሱም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠውን ሕግ በሚገባ የሚያውቅ የሕግ መምህር ነበር። የአምላኩ የእግዚአብሔር እጅ በርሱ ላይ ስለ ነበረች፣ የጠየቀውን ሁሉ ንጉሡ ፈቀደለት።
ጠላቶቻችን ሁሉ ይህን ሲሰሙ፣ በዙሪያችን ያሉ አሕዛብ ሁሉ ፈሩ፤ በራሳቸው መተማመንም አልቻሉም፤ ምክንያቱም ይህ ሥራ የተከናወነው በአምላካችን ርዳታ መሆኑን ተገንዝበዋል።
በዚያ ጊዜ አፋችን በሣቅ፣ አንደበታችንም በእልልታ ተሞላ፤ በዚያ ጊዜም በሕዝቦች መካከል፣ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገላቸው” ተባለ።
አስማተኞቹም ፈርዖንን፣ “ይህ የእግዚአብሔር ጣት ነው” አሉት፤ ነገር ግን የፈርዖን ልብ ደንድኖ ስለ ነበር፣ ልክ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው አልሰማቸው አለ።
እንዲህም ተባባሉ፤ “እንግዲህ እነዚህን ሰዎች ምን እናድርጋቸው? በኢየሩሳሌም የሚኖር ሁሉ በእነርሱ እጅ የተደረገውን ድንቅ ታምር ዐውቋል፣ ስለዚህ ይህን ማስተባበል አንችልም፤