መዝሙር 107:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የተቤዣቸው፣ ከጠላት እጅ የታደጋቸው ይህን ይበሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ የታደጋቸው፥ ከጠላትም እጅ ያዳናቸው ይናገሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የተቤዣቸው ከችግርም ያዳናቸው ሁሉ እንዲሁ ይበሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክብሬም ይመለስልኛል፥ በበገናና በመሰንቆ እነሣለሁ፤ ማልጄም እነሣለሁ፤ |
አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሕዝብህ እስከሚያልፉ ድረስ፣ የተቤዠሃቸው ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፣ ድንጋጤና ሽብር በእነርሱ ላይ ይመጣል፤ በክንድህ ብርታት፣ እንደ ድንጋይ የማይንቀሳቀሱ ይሆናሉ።
አሁን ግን፣ ያዕቆብ ሆይ የፈጠረህ፣ እስራኤል ሆይ! የሠራህ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ፤
የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ተጨነቂ፤ አሁንስ ከከተማ ወጥተሽ፣ በሜዳ ላይ መስፈር አለብሽና፤ ወደ ባቢሎን ትሄጃለሽ፤ በዚያ ከጠላት እጅ ትድኛለሽ። እግዚአብሔር በዚያ፣ ከጠላቶችሽ ይታደግሻል።
አንተም ራስህ በግብጽ ባሪያ እንደ ነበርህና አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ተቤዠህ አስታውስ፤ ይህን ትእዛዝ ዛሬ የምሰጥህም በዚሁ ምክንያት ነው።
ነገር ግን እናንተን በብርቱ እጅ ያወጣችሁ፣ ከባርነት ምድርና ከግብጽ ንጉሥ ከፈርዖን መዳፍ የተቤዣችሁ፣ እግዚአብሔር እናንተን ስለ ወደዳችሁና ለአባቶቻችሁ የማለላቸውን መሐላ ስለ ጠበቀ ነው።