ምሳሌ 9:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥበብ የለሽ ሴት ለፍላፊ ናት፤ እርሷም ስድና ዕውቀት የለሽ ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አላዋቂ ሴት ሁከተኛ ናት፥ አሳብ የላትም፥ አንዳችም አታውቅም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕውቀትን ማጣት፥ እንደ ለፍላፊ፥ ምንም ነገር እንደማታውቅ ደንቈሮና ኀፍረተቢስ ሴት መሆን ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰነፍና ነዝናዛ፥ እንጀራንም ያጣች ሴት ኀፍረትን የማታውቅ ትሆናለች። |
ያ ሰው በትዕቢት ተወጥሯል፤ አንዳችም አያስተውልም። ስለ ቃላት ለመከራከርና ለመጣላት ክፉ ጕጕት አለው፤ እነዚህም ቅናትን፣ ጥልን፣ ስድብን፣ መጥፎ ጥርጣሬን ያስከትላሉ፤