ምሳሌ 8:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከብር ይልቅ ምክሬን፣ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ ዕውቀትን ምረጡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተግሣጼን እንጂ ብርን አትቀበሉ፥ ከተመረጠ ወርቅም ይልቅ እውቀትን ተቀበሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብር ይልቅ ምክሬን ምረጡ፤ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ ዕውቀትን ምረጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብር ይልቅ ትምህርትን፥ ከተፈተነ ወርቅም ይልቅ ዕውቀትን ተቀበሉ። |
ጴጥሮስ ግን፣ “እኔ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ነገር ግን ያለኝን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥተህ በእግርህ ተመላለስ” አለው፤