ምሳሌ 6:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በልቡ ተንኰል ክፋትን የሚያውጠነጥን፣ ምን ጊዜም ጠብ ይጭራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠማማነት በልቡ አለ፥ ሁልጊዜም ክፋትን ያቅዳል፥ ጠብንም ይዘራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጠማማ አእምሮው ዘወትር ክፉ ነገርን ለማድረግ ያቅዳል፤ ሁልጊዜ ጠብን ይዘራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠማማ ልቡ ሁልጊዜ ክፋትን ያስባል፤ እንደዚህም ያለ ሰው ጠብን በከተማ ላይ ይዘራል። |
ክፉ ለመሥራት ለሚያቅዱ፣ በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ሲነጋ በማለዳ ይፈጽሙታል፤ የሚያደርጉበት ኀይል በእጃቸው ነውና።
ወንድሞች ሆይ፤ መለያየትን ከሚፈጥሩትና የተማራችሁትን ትምህርት በመቃወም በጕዟችሁ መሰናክል ከሚያደርጉት እንድትጠነቀቁ አሳስባችኋለሁ፤ ከእነርሱም ራቁ።