ምሳሌ 4:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ አትድረስ፤ አትጓዝበት፤ ሽሸው፤ መንገድህን ይዘህ ሂድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሷ ራቅ፥ አትሂድባትም፥ ራቅ በል ተዋትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእርሱ ራቅ፤ በዚያም አትራመድ፤ ከእርሱ ርቀህ በራስህ መንገድ ሂድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተጓዙበትም ቦታ አትሂድ፤ ከእነርሱ ፈቀቅ በል ተመለስም። |
በጽድቅ የሚራመድ፣ ቅን ነገር የሚናገር፣ በሽንገላ የሚገኝን ትርፍ የሚንቅ፣ መማለጃን ላለመቀበል እጁን የሚሰበስብ፣ የግድያን ሤራ ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ክፋትን ላለማየት ዐይኑን የሚጨፍን፣