ከዚያም ያዕቆብ እንዲህ ሲል ተሳለ፤ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋራ ቢሆን በምሄድበትም መንገድ ቢጠብቀኝ፣ የምበላው ምግብ፣ የምለብሰው ልብስ ቢሰጠኝ
ምሳሌ 30:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐሰትንና ሐሰት መናገርን ከእኔ አርቅልኝ፤ ድኽነትንም ሆነ ብልጽግናን አትስጠኝ፤ ብቻ የዕለት እንጀራዬን ስጠኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከንቱነትንና ሐሰተኛነትን ከእኔ አርቃቸው፥ ድህነትንና ሀብታምነትን አትስጠኝ፥ የሚያስፈልገኝን እንጀራ ስጠኝ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውን ከማታለልና ሐሰት ከመናገር ጠብቀኝ፤ የሚያስፈልገኝን ያኽል ምግብ ስጠኝ እንጂ ሀብታም ወይም ድኻ አታድርገኝ። |
ከዚያም ያዕቆብ እንዲህ ሲል ተሳለ፤ “እግዚአብሔር ከእኔ ጋራ ቢሆን በምሄድበትም መንገድ ቢጠብቀኝ፣ የምበላው ምግብ፣ የምለብሰው ልብስ ቢሰጠኝ
እስራኤላውያንም ይህን ባዩ ጊዜ ምን እንደ ሆነ ባለማወቃቸው እርስ በርሳቸው፣ “ይህ ነገር ምንድን ነው?” ተባባሉ። ሙሴም፣ “ይህ ትበሉት ዘንድ እግዚአብሔር የሰጣችሁ እንጀራ ነው አላቸው።
የሰበሰቡትን በጎሞር በሰፈሩ ጊዜ፣ ብዙ የሰበሰበ አላተረፈም፤ ጥቂትም የሰበሰበ አልጐደለበትም፤ እያንዳንዱ የሰበሰበው የሚያስፈልገውን ያህል ሆነ።
እግዚአብሔር ሰንበትን የሰጣችሁ መሆኑን ልብ በሉ፤ በስድስተኛው ቀን ለሁለት ቀን የሚሆን እንጀራ የሰጣችሁ ለዚህ ነው። በሰባተኛው ቀን እያንዳንዱ ሰው ባለበት ይቈይ፤ ማንም አይወጣም።”
ፍትሕን የሚጠራ ማንም የለም፤ ጕዳዩን በቅንነት የሚያቀርብ የለም፤ በከንቱ ነገር ታመኑ፤ ሐሰትን ተናገሩ፤ ሁከትን ፀነሱ፤ ክፋትንም ወለዱ።
ንጉሡም ሴዴቅያስ፣ ኤርምያስ በዘብ ጠባቂዎች አደባባይ እንዲቀመጥና በከተማዪቱ ያለው እንጀራ እስኪያልቅ ድረስ ከእንጀራ ጋጋሪዎች ሰፈር በየቀኑ አንድ አንድ እንጀራ እንዲሰጠው አዘዘ፤ ስለዚህ ኤርምያስ በዘብ ጠባቂዎች አደባባይ ተቀመጠ።
“እናንተ ሰዎች፤ ለምን ይህን ታደርጋላችሁ? እኛም እኮ እንደ እናንተው ሰዎች ነን። እናንተም ደግሞ ከነዚህ ከንቱ ነገሮች ርቃችሁ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር እንድትመለሱ ወንጌልን እንሰብክላችኋለን።