ምሳሌ 26:27 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጕድጓድ የሚምስ ራሱ ይገባበታል፤ ድንጋይ የሚያንከባልልም ተመልሶ በላዩ ላይ ይገለበጥበታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉድጓድን የሚምስ ይወድቅበታል፥ ድንጋይንም የሚያንከባልል ይገለበጥበታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሌሎች ወጥመድን የሚዘረጉ ሰዎች ራሳቸው ይያዙበታል፤ በሰው ላይ የሚሰዱት የድንጋይ ናዳ እነርሱን መልሶ ይጐዳቸዋል። |
ሤራው በንጉሡ ዘንድ እንደ ታወቀ ሐማ በአይሁድ ላይ የሸረበው ሤራ በገዛ ራሱ ላይ እንዲጠመጠም፣ እርሱና ወንዶች ልጆቹም በዕንጨት ላይ እንዲሰቀሉ የጽሑፍ ትእዛዝ አስተላለፈ።
ኢየሩሳሌም ተንገዳግዳለች፤ ይሁዳም ለመውደቅ ተቃርባለች፤ ንግግራቸውም ሆነ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን የሚቃወም፣ የክብሩንም መገኘት የሚያቃልል ነውና።