ከግልፍተኛ ጋራ ወዳጅ አትሁን፤ በቀላሉ ቱግ ከሚልም ሰው ጋራ አትወዳጅ፤
ከቁጡ ሰው ጋር ባልንጀራ አትሁን፥ ከንዴተኛም ጋር አትሂድ፥
ከንዴተኛና ከቊጡ ሰው ጋር ባልንጀራ አትሁን፤
ከቍጡ ሰው ጋር ባልንጀራ አትሁን፥ ከነዝናዛም ጓደኛ ጋር አትኑር።
ከጠቢብ ጋራ የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ የሞኝ ባልንጀራ ግን ጕዳት ያገኘዋል።
ግልፍተኛ ሰው ጠብ ያነሣሣል፤ ታጋሽ ሰው ግን ጠብን ያበርዳል።
ትዕቢተኛና ኵሩ ሰው “ፌዘኛ” ይባላል፤ በጠባዩም እብሪተኛ ነው።
ቍጡ ሰው ጠብን ይጭራል፤ ግልፍተኛም ብዙ ኀጢአት ይሠራል።