ምሳሌ 21:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሐሰተኛ አንደበት የተገኘ ሀብት፣ በንኖ የሚጠፋ ተን፣ ለሞትም የሚያበቃ ወጥመድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሐሰተኛ ምላስ መዝገብ ማከማቸት የሚበንን ጉም ነው፥ ይህን የሚፈልጉ ሞትን ይፈልጋሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመዋሸት የሚገኝ ሀብት ተኖ እንደሚጠፋ እንፋሎትና እንደሚገድል ወጥመድ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሐሰተኛ ምላስ ሀብትን የሚያከማች ከንቱ ነገርን ይከተላል፥ ወደ ሞት ወጥመድም ያደርሰዋል። |
ሀብትን በግፍ የሚያከማች ሰው፣ ያልፈለፈለችውን ጫጩት እንደምትታቀፍ ቆቅ ነው፤ በዕድሜው አጋማሽ ትቶት ይሄዳል፤ በመጨረሻም ሞኝነቱ ይረጋገጣል።
እነዚህን ዝም ማሠኘት ተገቢ ነው፤ ምክንያቱም ትክክል ባልሆነ መንገድ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ማስተማር የማይገባቸውን ነገር በማስተማር ቤተ ሰብን ሁሉ በመበከል ላይ ናቸው።