ምሳሌ 20:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክር ጠይቀህ ዕቅድ አውጣ፤ ጦርነት የምትገጥም ከሆነ መመሪያ ተቀበል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሳብ በምክር ትጸናለች፥ በመልካምም ምክር ሰልፍ አድርግ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልካም ምክርን ብትቀበል ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ ስለዚህ መልካም ምክር ሳትቀበል ወደ ጦርነት አትሂድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐሳብ በምክር ትጸናለች፥ በመልካምም ምክር ሰልፍ አድርግ። |
“ወይም አንድ ንጉሥ ከሌላው ንጉሥ ጋራ ጦርነት ሊገጥም በሚነሣበት ጊዜ፣ ሃያ ሺሕ ሰራዊት አስከትቶ የሚመጣበትን ንጉሥ፣ በዐሥር ሺሕ ሰራዊት መመከት እንደሚችል ተቀምጦ የማይመክር ማን ነው?
ያየም ሁሉ፣ “እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ ጀምሮ እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አልታየም፤ አልተደረገም፤ ምን ማድረግ እንዳለብንም በነገሩ አስቡበት፤ ተመካከሩበት” ተባባሉ።
እስራኤላውያን ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግዚአብሔርም፣ “ብንያማውያንን ለመውጋት ከመካከላችን ማን ቀድሞ ይውጣ?” ሲሉ ጠየቁ። እግዚአብሔርም፣ “ይሁዳ ቀድሞ ይውጣ” ብሎ መለሰ።
እስራኤላውያን ወጥተው እስኪመሽ ድረስ በእግዚአብሔር ፊት አለቀሱ፤ “ወንድሞቻችንን ብንያማውያንን ለመግጠም እንደ ገና እንውጣን?” ብለው እግዚአብሔርን ጠየቁ። እግዚአብሔርም፣ “አዎን፤ ውጡና ግጠሟቸው” ብሎ መለሰላቸው።