ምሳሌ 2:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅኖች በምድሪቱ ይቀመጣሉና፤ ነቀፋ የሌለባቸውም በርሷ ላይ ጸንተው ይኖራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅኖች በምድር ላይ ይቀመጣሉና፥ ፍጹማንም በእርሷ ይኖራሉና፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህች ምድር መኖር የሚችሉት ልበ ቅኖችና ደጋግ ሰዎች ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደጋግ ሰዎች በምድር ላይ ይቀመጣሉ፥ ጻድቃንም በእርስዋ ይኖራሉ፤ |
እግዚአብሔርም ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛውን የኢዮብን ሕይወት ባረከ። እርሱም ዐሥራ አራት ሺሕ በጎች፣ ስድስት ሺሕ ግመሎች፣ አንድ ሺሕ ጥማድ በሬዎች፣ አንድ ሺሕ እንስት አህዮችም ነበሩት።
እግዚአብሔር አምላክ ፀሓይና ጋሻ ነውና፤ እግዚአብሔር ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ያለ ነቀፋ የሚሄዱትን፣ መልካም ነገር አይነፍጋቸውም።