ምሳሌ 18:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕመም ጊዜ፣ ሰውን መንፈሱ ትደግፈዋለች፤ የተሰበረውን መንፈስ ግን ማን ሊሸከም ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ነፍስ ሕመሙን ይታገሣል፥ የተቀጠቀጠን መንፈስ ግን ማን ያጠንክረዋል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠንካራ መንፈስ ሕመምን ያስታግሣል፤ መንፈሱ የደከመውን ግን ማንም አይረዳውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብልህ አገልጋይ የጌታውን ቍጣ ያበርዳል፥ አእምሮ የጐደለውን ሰው ማን ይችለዋል? |
እንግዲህ ትምክሕታችን ይህ ነው፤ በዚህ ዓለም በተለይም ከእናንተ ጋራ ባለን ግንኙነት፣ ከእግዚአብሔር በሆነ ቅድስናና ቅንነት እንደ ኖርን ኅሊናችን ይመሰክራል፤ ይህም በሰው ጥበብ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ጸጋ ነው።