ምሳሌ 17:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሞኝ ልጅ መውለድ ሐዘን ያስከትላል፤ የተላላም አባት ደስታ የለውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰነፍን የሚወልድ ኀዘን ይሆንበታል፥ የደንቆሮ ልጅም አባት ደስ አይለውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰነፍ ልጅ አባት ከሐዘንና ከብስጭት በቀር ምንም ደስታ የለውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰነፍ ልብ ገንዘብ ላደረጋት ኀዘን ናት፥ አባት ባልተማረ ልጁ ደስ አይለውም፥ ብልህ ልጅ ግን እናቱን ደስ ያሰኛል። |
ንጉሡም እጅግ ዐዘነ፤ በቅጽር በሩ ዐናት ላይ ወዳለችው ቤት ወጥቶ አለቀሰ፤ ሲሄድም፣ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! በአንተ ፈንታ ምነው እኔ በሞትሁ ኖሮ! አቤሴሎም ሆይ፤ ልጄን! ወየው ልጄን!” ይል ነበር።
ባለፈው ጊዜ እንደዚያ የጻፍሁላችሁ ወደ እናንተ ስመጣ ደስ ሊያሠኙኝ የሚገባቸው ሰዎች እንዳያሳዝኑኝ በማለት ነው፤ ምክንያቱም የእኔ ደስታ የሁላችሁ ደስታ እንደሚሆን አምናለሁ።