ምሳሌ 16:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዐይኑ የሚጠቅስ ሰው ጠማማነትን ያውጠነጥናል፤ በከንፈሩ የሚያሽሟጥጥም ወደ ክፋት ያዘነብላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓይኑን የሚዘጋ ጠማማ አሳብን ያስባል፥ ከንፈሩን የሚነክስ ክፋትን ይፈጽማል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐይኑን በሰው ላይ የሚጠቅስ ተንኰልን ያቀደ ነው፤ ከንፈሩንም የሚነክስ ወደ ክፋት የሚያመራ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዐይኑ ትኩር ብሎ የሚመለከት፥ ጠማማ ዐሳብን ያስባል፤ በከንፈሩም ክፉውን ሁሉ የሚያደርግ የክፋት ምድጃ ነው። |
የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፤ ጆሯቸውን ድፈን፤ ዐይኖቻቸውንም ክደን፤ ይህ ካልሆነማ፣ በዐይናቸው አይተው፣ በጆሯቸው ሰምተው፣ በልባቸውም አስተውለው በመመለስ ይፈወሳሉ።”
እጆቹ ክፉ ለማድረግ ሠልጥነዋል፤ ገዥው እጅ መንሻ ይፈልጋል፤ ፈራጁ ጕቦ ይቀበላል፤ ኀይለኞች ያሻቸውን ያስፈጽማሉ፤ ሁሉም አንድ ላይ ያሤራሉ።
የሕዝቡ ልብ ደንድኗልና፤ ጆሯቸውም አይሰማም፤ እንዳያዩም ዐይናቸውን ጨፍነዋል፤ ይህ ባይሆን ኖሮ፣ በዐይናቸው አይተው፣ በጆሯቸው ሰምተው፣ በልባቸውም አስተውለው፣ ወደ እኔ በተመለሱና በፈወስኋቸው ነበር።’