ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ። ብርቱዎች እንድትሆኑ፣ የምድሪቱን መልካም ነገር እንድትበሉና ለልጆቻችሁም የዘላለም ርስት እንድታወርሱ ከእነርሱ ጋራ ምንም ዐይነት ውል አታድርጉ’ ብለህ የሰጠኸውን ትእዛዝ ነው።
ምሳሌ 13:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግ ሰው ለልጅ ልጆቹ ውርስ ትቶ ያልፋል፤ የኀጢአተኞች ሀብት ግን ለጻድቃን ይከማቻል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጻድቅ ሰው ለልጅ ልጆቹ ያወርሳል፥ የኃጢአተኛ ብልጥግና ግን ለጻድቅ ትጠበቃለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግ ሰው ለልጅ ልጆቹ የሚተላለፍ ሀብት ያገኛል፤ የኃጢአተኞችን ሀብት ግን ቅን ሰዎች ይወርሱታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግ ሰው ለልጅ ልጅ ያወርሳል፥ የኀጢአተኞች ብልጽግና ግን ለጻድቃን ይደልባል። |
ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ። ብርቱዎች እንድትሆኑ፣ የምድሪቱን መልካም ነገር እንድትበሉና ለልጆቻችሁም የዘላለም ርስት እንድታወርሱ ከእነርሱ ጋራ ምንም ዐይነት ውል አታድርጉ’ ብለህ የሰጠኸውን ትእዛዝ ነው።
አምላክ፣ ደስ ለሚያሠኘው ሰው ጥበብን፣ ዕውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል። ለኀጢአተኛ ግን፣ አምላክን ደስ ለሚያሠኘው ይተውለት ዘንድ፣ ሀብትን የመሰብሰብና የማከናወን ተግባር ይሰጠዋል። ይህም ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።