ምሳሌ 13:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምኞት ስትፈጸም ነፍስን ደስ ታሰኛለች፤ ሞኞች ግን ከክፋት መራቅን ይጸየፋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተፈጸመች ፈቃድ ሰውነትን ደስ ታሰኛለች፥ ሰነፎች ግን ከክፉ መራቅን ይጸየፋሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተመኙትን ነገር ማግኘት እጅግ ደስ ያሰኛል፤ ማስተዋል የጐደላቸው ሰዎች ግን ከክፉ ነገር መራቅ አይፈልጉም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የደጋግ ሰዎች ምኞት ነፍስን ያድናል፤ የሰነፎች ሥራ ግን ከዕውቀት የራቀ ነው። |
ከእነርሱ ጥቂት ዕልፍ እንዳልሁ፣ ውዴን አገኘሁት፤ ያዝሁት፤ ወደ እናቴ ቤት እስካመጣው፣ በማሕፀን ወደ ተሸከመችኝም ዕልፍኝ እስካገባው ድረስ አልለቀውም።
ይሁን እንጂ፣ “ጌታ የርሱ የሆኑትን ያውቃል” ደግሞም፣ “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከክፋት ይራቅ” የሚል ማኅተም ያለበት የማይነቃነቅ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሟል።