ከጥቂት ሰዎች ጋራ በሌሊት ወጣሁ። ለኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ አምላኬ በልቤ ያኖረውን ነገር ለማንም አልነገርሁም፤ ከተቀመጥሁበት እንስሳ በቀር ከእኔ ጋራ ሌሎች እንስሳት አልነበሩም።
ምሳሌ 12:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስተዋይ ሰው ዕውቀቱን ይሰውራል፤ የሞኞች ልብ ግን ቂልነትን ይነዛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብልህ ሰው እውቀትን ይሸሽጋል፥ የሰነፎች ልብ ግን ስንፍናን ያወራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አስተዋይ ሰዎች “ዐዋቂዎች ነን” እያሉ አይመጻደቁም፤ ሞኞች ግን “ዐዋቂዎች ነን” በማለት ድንቊርናቸውን ይገልጣሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብልህ ሰው የጥበብ መንበር ነው፤ የሰነፎች ልብ ግን መርገምን ያገኛል። |
ከጥቂት ሰዎች ጋራ በሌሊት ወጣሁ። ለኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ አምላኬ በልቤ ያኖረውን ነገር ለማንም አልነገርሁም፤ ከተቀመጥሁበት እንስሳ በቀር ከእኔ ጋራ ሌሎች እንስሳት አልነበሩም።
ለአይሁድ ወይም ለካህናቱ ወይም ለመኳንንቱ ወይም ለሹማምቱ ወይም ሥራውን ለሚሠሩት ሰዎች ገና ምንም የተናገርሁት ነገር ስላልነበረ፣ ወዴት እንደ ሄድሁ ወይም ምን እንዳደረግሁ ሹማምቱ አላወቁም።