በጎ ነገርን ተግቶ የሚሻ በጎ ነገር ይጠብቀዋል፤ ክፉ ነገር የሚፈልገውን ግን ክፉ ያገኘዋል።
መልካምን ተግቶ የሚሻ ደስታን ይፈልጋል፥ ክፉን በሚፈልግ ግን ክፉ ይመጣበታል።
መልካምን ነገር ተግቶ የሚሻ መልካም ነገርን ያገኛል፤ ክፉ ነገርን የሚሠራ ግን ክፉ ነገር ይደርስበታል።
መልካምን የሚያስብ መልካም ክብርን ይወድዳል። ክፋትን የሚፈልግን ግን ክፋት ታገኘዋለች።
ስለዚህ ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው ግንድ ላይ ሐማን ሰቀሉት፤ ከዚያም የንጉሡ ቍጣ በረደ።
ክፉዎች የተጨነቀውን በእብሪት ያሳድዳሉ፤ በወጠኑት ተንኰል ይጠመዱ።
ለእግሬ ወጥመድን ዘረጉ፤ ነፍሴንም አጐበጧት፤ በመተላለፊያዬ ላይ ጕድጓድ ቈፈሩ፤ ነገር ግን ራሳቸው ገቡበት። ሴላ
ክፉ ሰው ዐመፅን ብቻ ይፈልጋል፤ በርሱም ላይ ጨካኝ መልእክተኛ ይላክበታል።
ቸር ሰው ራሱ ይባረካል፤ ምግቡን ከድኾች ጋራ ይካፈላልና።