ምሳሌ 10:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጻድቃን ከንፈሮች ተገቢውን ነገር ያውቃሉ፤ የክፉዎች አንደበት ግን የሚያውቀው ጠማማውን ብቻ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቅ ከንፈሮች ደስ የሚያሰኝ ነገርን ያውቃሉ፥ የክፉዎች አፍ ግን ጠማማ ነገር ይናገራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደጋግ ሰዎች ንግግር ተስማሚ ነው፤ የክፉዎች ንግግር ግን ጠማማ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጻድቃን ከንፈሮች ሞገስን ያፈስሳሉ፤ የኃጥኣን አፍ ግን ከዕውቀት ይከለከላል። |
ስለዚህ ንጉሥ ሆይ፤ ምክሬን ስማ፤ ኀጢአት መሥራትን ትተህ ትክክለኛ የሆነውን አድርግ፤ ክፋትን ትተህ ለተጨቈኑት ቸርነትን አድርግ፤ ምናልባት በሰላም የምትኖርበት ዘመን ይራዘምልህ ይሆናል።”