ምሳሌ 10:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከቃላት ብዛት ኀጢአት አይታጣም፤ አንደበቱን የሚገታ ግን ጠቢብ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቃል ብዛት ውስጥ መተላለፍ ሳይኖር አይቀርም፥ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብዙ ንግግር ውስጥ ስሕተት አይጠፋም፤ ስለዚህ አስተዋይ ሰው ብዙ ከመናገር ይቈጠባል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኃጥእ ከነገር ብዛት የተነሣ ከኀጢአት አያመልጥም፤ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው። |
ወደ እግዚአብሔር ቤት ስትሄድ እግርህን ጠብቅ። ለመስማት መቅረብ የሞኞችን መሥዋዕት ከማቅረብ ይበልጣል፤ እነርሱ ክፉ እንደሚሠሩ አያውቁምና።
በአፍህ አትፍጠን፤ በአምላክም ፊት ማንኛውንም ነገር ለመናገር፣ በልብህ አትቸኵል፤ አምላክ በሰማይ፣ አንተ ደግሞ በምድር ነህ፤ ስለዚህ ቃልህ ጥቂት ይሁን።