ምሳሌ 1:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያላግባብ ለጥቅም የሚሯሯጡ ሁሉ መጨረሻቸው እንዲህ ነው፤ የሕይወታቸው መጥፊያም ይኸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግፍ ማትረፍ የሚፈልግ ሁሉ መንገዱ እንዲሁ ነው። የግፉ ባለቤትም ነፍስ ይነጠቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕገ ወጥ መንገድ ሀብትን የሚሰበስቡ ሰዎች ያ የሰበሰቡት ሀብት ሕይወታቸውን ያጠፋዋል። በግፍም የሚበለጽጉ ሰዎች ዕድል ፈንታቸው ይኸው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህ መንገድ ኀጢአትን የሚፈጽሙ ሁሉ ነው። ቅሚያ ነፍሳቸውን ታጠፋለች። |
ከምርኮው ዕቃ መካከል ከሰናዖር የመጣ አንድ የሚያምር ካባ፣ ሁለት መቶ ሰቅል ብርና ክብደቱ ዐምሳ ሰቅል የሚሆን የወርቅ ቡችላ አይቼ ጐመጀሁ፤ ወሰድኋቸውም፤ ዕቃውም ብሩ ከታች ሆኖ፣ በድንኳኔ ውስጥ መሬት ተቀብሯል።”
ኢያሱም፣ “እንዲህ ያለውን መከራ ለምን አመጣብህን? እነሆ፤ ዛሬ በአንተም ላይ እግዚአብሔር መከራ ያመጣብሃል” አለው። ከዚያም እስራኤል በሙሉ በድንጋይ ወገሩት፤ የቀሩትንም እንደዚሁ ከወገሩ በኋላ በእሳት አቃጠሏቸው።