ምሳሌ 1:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጄ ሆይ፤ ዐብረሃቸው አትሂድ፤ በሚሄዱበትም መንገድ እግርህን አታንሣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጄ ሆይ፥ ከእነርሱ ጋር በመንገድ አትሂድ፥ ከጎዳናቸውም እግርህን አርቅ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጄ ሆይ! እነዚህን ከመሰሉ ሰዎች ጋር አብረህ አትሂድ፤ ከእነርሱም ራቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጄ ሆይ፥ ከእነርሱ ጋር በመንገድ አትሂድ፥ ከጎዳናቸውም እግርህን ፈቀቅ አድርግ፤ |
በጽድቅ የሚራመድ፣ ቅን ነገር የሚናገር፣ በሽንገላ የሚገኝን ትርፍ የሚንቅ፣ መማለጃን ላለመቀበል እጁን የሚሰበስብ፣ የግድያን ሤራ ላለመስማት ጆሮውን የሚደፍን፣ ክፋትን ላለማየት ዐይኑን የሚጨፍን፣
እግዚአብሔር ስለዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፤ “መቅበዝበዝ እጅግ ይወድዳሉ፤ እግሮቻቸው አይገቱም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር በእነርሱ ደስ አይለውም፤ አሁን በደላቸውን ያስባል፤ በኀጢአታቸውም ይቀጣቸዋል።”