ገባዖናውያንም፣ “ከሳኦልም ሆነ ከቤተ ሰቡ ብር ወይም ወርቅ የመጠየቅ መብት የለንም፤ እንዲሁም ከእስራኤል ማንንም ለመግደል መብት የለንም” ብለው መለሱለት። ዳዊትም፣ “ታዲያ ምን ላድርግላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው።
ዘኍል 35:32 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ወደ መማጸኛ ከተማ ሸሽቶ ስለ ገባ ስለ ማንኛውም ሰው የደም ዋጋ በመቀበል ሊቀ ካህናቱ ከመሞቱ በፊት ወደ አገሩ ተመልሶ ሄዶ እዚያ እንዲኖር አታድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታላቁ ካህን ሳይሞት ወደ ምድሩ እንዲመለስ ወደ መማፀኛው ከተማ ከሸሸው ሰው የነፍስ ዋጋ አትቀበሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው ወደ መማጸኛ ከተማ ሸሽቶ ቢያመልጥ ሊቀ ካህናቱ ከመሞቱ በፊት ወደ ቤቱ መመለስ ይችል ዘንድ ገንዘብ እንዲከፍል አትፍቀዱለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታላቁ ካህን እስኪሞት ወደ ምድሩ ትመልሱት ዘንድ ወደ መማፀኛው ከተማ ከሸሸው ዋጋ አትቀበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዋነኛው ካህን ሳይሞት ወደ ምድሩ ይመለስ ዘንድ ወደ መማፀኛው ከተማ ከሸሸው የነፍስ ዋጋ አትቀበሉ። |
ገባዖናውያንም፣ “ከሳኦልም ሆነ ከቤተ ሰቡ ብር ወይም ወርቅ የመጠየቅ መብት የለንም፤ እንዲሁም ከእስራኤል ማንንም ለመግደል መብት የለንም” ብለው መለሱለት። ዳዊትም፣ “ታዲያ ምን ላድርግላችሁ?” ሲል ጠየቃቸው።
“ ‘ደም ምድሪቱን ስለሚያረክሳት፣ ደም ለፈሰሰባትም ምድር ስርየት ሊደረግላት የሚችለው በሌላ ሳይሆን በዚያው ደሙን ባፈሰሰው ሰው ደም ብቻ በመሆኑ፣ የምትኖሩባትን ምድር በደም አታርከሷት፤
መጽሐፍ ግን ዓለም ሁሉ የኀጢአት እስረኛ መሆኑን ያውጃል፤ ይኸውም በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው ተስፋ ለሚያምኑት ሁሉ ይሰጥ ዘንድ ነው።
እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤ “መጽሐፉን ልትወስድ፣ ማኅተሞቹንም ልትፈታ ይገባሃል፤ ምክንያቱም ታርደሃል፤ በደምህም ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋ ሁሉ፣ ከወገን ሁሉ፣ ከሕዝብ ሁሉ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ዋጅተሃል።