ዘኍል 35:24 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማኅበሩ በዚህ ሰውና በደመኛው መካከል በእነዚህ ደንቦች መሠረት ይፍረድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማኅበሩ በመቺውና በደም ተባቃዩ መካከል ፍርድን በዚህ መሠረት ይፍረድ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህ ያለው ሁኔታ በሚፈጸምበት ጊዜ ማኅበሩ በገዳዩና በተበቃዩ መካከል ፍርድ የሚሰጠው በሚከተለው ሥርዓት መሠረት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠላቱም ባይሆን፥ ክፉም ያደርግበት ዘንድ ባይሻ፥ ማኅበሩ በመቺውና በባለ ደሙ መካከል ፍርድን እንደዚህ ይፍረዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማኅበሩ በመቺውና በደም ተባቃዩ መካከል ፍርድን እንደዚሁ ይፍረድ፤ |
ማኅበሩም በነፍሰ ገዳይነት የተከሰሰውን ሰው ከደመኛው እጅ በማስጣል ወደ ሸሸበት ወደ መማጸኛው ከተማ ይመልሰው፤ የተቀደሰ ዘይት የተቀባው ሊቀ ካህን እስኪሞትም ድረስ በዚያ ይቈይ።
በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስኪቀርብና በዚያ ጊዜ የሚያገለግለው ሊቀ ካህናት እስኪሞት ድረስ በዚያች ከተማ ይቈይ። ከዚያም ወደ ቤቱ፣ ሸሽቶ ወደ መጣበት ከተማ ሊመለስ ይችላል።”