ዘኍል 33:49 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እዚያም በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ በሞዓብ ሜዳ ከቤትየሺሞት እስከ አቤልስጢም ባለው ስፍራ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዮርዳኖስም አጠገብ በሞዓብ ሜዳ ላይ ከቤትየሺሞት እስከ አቤልሰጢም ድረስ ሰፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዮርዳኖስም አጠገብ በሞአብ ሜዳ ላይ ከቤትየሺሞት እስከ አቤል ሹቲም ድረስ ሰፈሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዮርዳኖስም አጠገብ በሞዓብ ምዕራብ ከአሲሞት መካከል እስከ አቤልሰጢም ድረስ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዮርዳኖስም አጠገብ በሞዓብ ሜዳ ላይ ከቤትየሺሞት እስከ አቤልሰጢም ድረስ ሰፈሩ። |
ከዚያም የነዌ ልጅ ኢያሱ፣ “ሄዳችሁ ምድሪቱን፣ በተለይም የኢያሪኮን ከተማ ሰልሉ” ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላከ፤ ሰዎቹም ሄደው ረዓብ ከተባለች ጋለሞታ ቤት ገቡ፤ በዚያም ዐደሩ።