ስለዚህ ሄደው የከተማዪቱን መግቢያ በር ጠባቂዎች ጮኸው በመጥራት፣ “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ገባን፤ እዚያም ከታሰሩ ፈረሶችና አህዮች በቀር አንድም ሰው አልነበረም፤ የማንም ድምፅ አልተሰማም፤ ድንኳኖቹም እንዳሉ ናቸው” ብለው ነገሯቸው።
ነህምያ 7:73 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ በር ጠባቂዎቹ፣ መዘምራኑና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሕዝቡም የተወሰነው ክፍልና የቀሩት እስራኤላውያን በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ። ሰባተኛው ወር በደረሰና እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው በተቀመጡ ጊዜ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ የቤተ መቅደስ ዘብ ጠባቂዎቹ፥ መዘምራኑ፥ ከሕዝቡም አንዳንድ ሰዎች የቤተ መቅደስ አገልጋዮች፥ በአጠቃላይ እስራኤላውያን ሁሉ በየከተሞቻቸው ሰፈሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህናቱና ሌዋውያኑም፥ በረኞቹና መዘምራኑም፥ ከሕዝቡም ዐያሌዎቹ፥ ናታኒምም፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህናቱና ሌዋውያኑም፥ በረኞቹና መዘምራኑም ከሕዝቡም አያሌዎቹ፥ ናታኒምም፥ እስራኤልም ሁሉ በከተሞቻቸው ተቀመጡ። |
ስለዚህ ሄደው የከተማዪቱን መግቢያ በር ጠባቂዎች ጮኸው በመጥራት፣ “ወደ ሶርያውያን ሰፈር ገባን፤ እዚያም ከታሰሩ ፈረሶችና አህዮች በቀር አንድም ሰው አልነበረም፤ የማንም ድምፅ አልተሰማም፤ ድንኳኖቹም እንዳሉ ናቸው” ብለው ነገሯቸው።
በመጀመሪያ በየርስታቸውና በየከተሞቻቸው ተመልሰው የሰፈሩት ጥቂት እስራኤላውያን፣ ካህናት፣ ሌዋውያንና በቤተ መቅደሱ ውስጥ የጕልበት ሥራ የሚሠሩ አገልጋዮች ነበሩ።
ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ መዘምራኑ፣ በር ጠባቂዎቹና የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች፣ ከሌሎች ሰዎች ጋራ በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ፤ የቀሩት እስራኤላውያንም በየራሳቸው ከተሞች ሰፈሩ።
እንግዲህ በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የአውራጃዪቱ መሪዎች እነዚህ ናቸው፤ በዚህ ጊዜም በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩ የተወሰኑ እስራኤላውያን፣ ካህናት፣ ሌዋውያን፣ የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና የሰሎሞን አገልጋዮች ዘሮች እያንዳንዳቸው በተለያዩ ከተሞች ባለ በየራሳቸው ንብረት ላይ ተቀመጡ፤