ከእኔ በፊት የነበሩት የቀድሞዎቹ አገረ ገዦች ግን ከምግቡና ከወይኑ ሌላ፣ በሕዝቡ ላይ ከባድ ሸክም በመጫን አርባ ሰቅል ብር ይወስዱ ነበር፤ ረዳቶቻቸውም እንዲሁ ይጭኑባቸው ነበር። እኔ ግን እግዚአብሔርን ከመፍራቴ የተነሣ እንዲህ ያለውን አላደረግሁም።
ነህምያ 5:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ ይልቅ ራሴን ለዚህ ቅጥር ሥራ ሰጠሁ። ሰዎቼም ሁሉ ለሥራው እዚያው ይሰበሰቡ ነበር፤ ምንም መሬት አልነበረንም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተጨማሪም ለዚህ የቅጥር ሥራ እራሴን ሰጠሁ፥ እርሻም አልገዛንም፤ አገልጋዮቼም ሁሉ ወደዚያው ወደ ሥራው ተሰበሰቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያለኝን ኀይል ሁሉ የኢየሩሳሌምን ቅጽር እንደገና በማሳነጽ ተግባር ላይ አዋልኩት እንጂ ለግሌ ምንም ዐይነት ንብረት አልሰበሰብኩም፤ አገልጋዮቼም ሁሉ በዚህ ሥራ ተባበሩኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም የቅጥሩን ሥራ ሠራሁ፤ እርሻም አልገዛሁም፤ ብላቴኖችም ሁሉ ወደዚያው ወደ ሥራው ተሰበሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም አጥብቄ የቅጥሩን ሥራ ሠራሁ፥ እርሻም አልገዛንም፥ ብላቴኖቼም ሁሉ ወደዚያው ወደ ሥራው ተሰበሰቡ። |
ከእኔ በፊት የነበሩት የቀድሞዎቹ አገረ ገዦች ግን ከምግቡና ከወይኑ ሌላ፣ በሕዝቡ ላይ ከባድ ሸክም በመጫን አርባ ሰቅል ብር ይወስዱ ነበር፤ ረዳቶቻቸውም እንዲሁ ይጭኑባቸው ነበር። እኔ ግን እግዚአብሔርን ከመፍራቴ የተነሣ እንዲህ ያለውን አላደረግሁም።
ሙሴም በጣም ተቈጣ፤ እግዚአብሔርንም “ቍርባናቸውን አትቀበል፤ እኔ ከእነዚህ ሰዎች የወሰድሁት አንድ አህያ እንኳ የለም፤ አንዳቸውንም አልበደልሁም” አለ።
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ፤ ምክንያቱም ለጌታ የምትደክሙት በከንቱ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።