ነህምያ 3:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ደግሞ የሌላው የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዥ የኤንሐዳድ ልጅ በዋይና በርሱም ሥር የነበሩት የአገሩ ሰዎች መልሰው ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም በኋላ ወንድሞቻቸው፥ የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዚ የሆነው የሔናዳድ ልጅ ባዋይ አደሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም ቀጥሎ ያለውን ክፍል የሌላው የቀዒላ ወረዳ እኩሌታ ገዢ የሆነው የሔናዳድ ልጅ ባዋይ ሠራው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም በኋላ የቅዔላ ግዛት እኩሌታ ገዢ የኤንሐዳድ ልጅ ቤኒይና ወንድሞቹ ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም በኋላ የቅዒላ ግዛት እኩሌታ አለቃ የኤንሐዳድ ልጅ በዋይ ወንድሞቹም አደሱ። |
ከርሱ ቀጥሎ ሌዋውያኑ በባኒ ልጅ በሬሁ ሥር ሆነው የዕድሳት ሥራ ሠሩ። ከርሱ ቀጥሎ የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዥ ሐሸብያ አውራጃውን መልሶ ሠራ።
ከርሱም ቀጥሎ ወደ ጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት በሚያወጣውና እስከ ማእዘኑ በሚደርሰው ትይዩ ያለውን ሌላ ክፍል የምጽጳ ገዥ የኢያሱ ልጅ ኤጽር መልሶ ሠራ።