ነህምያ 2:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሌሊትም ወጥቼ በሸለቆው በር በኩል አድርጌ ወደ ዘንዶው የውሃ ጕድጓድና ወደ ቈሻሻ መድፊያው በር ሄድሁ፤ የፈረሱትንም የኢየሩሳሌምን ቅጥሮችና በእሳት የወደሙትን በሮች ተመለከትሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሌሊትም በሸለቆው በር ወጣሁ፥ ወደ “የዘንዶ ምንጭ” እና ወደ “የፍግ በር” ሄድኩ፤ የፈረሰውን የኢየሩሳሌምን ቅጥርና በእሳት የተቃጠሉትን በሮችዋን ተመለከትኩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሸለቆ ቅጽር በር ወጥቼ የዘንዶ ምንጭ ተብሎ የሚጠራውን ስፍራ በማለፍ፥ በስተ ደቡብ ወደሚገኘው የጒድፍ መጣያ ተብሎ ወደሚጠራው ስፍራ ሄድኩ፤ ጊዜውም ገና ሌሊት ነበር፤ በማልፍበትም ጊዜ የፈራረሱትን የከተማይቱን ቅጽሮችና በእሳት የወደሙትን የቅጽር በሮች ጐበኘሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሸለቆውም በር ወጣሁ፤ ወደ በለስም ምንጭና ወደ ጕድፍ መጣያው በር ሄድሁ፤ የፈረሰውንም የኢየሩሳሌምን ቅጥር፥ በእሳትም የተቃጠሉትን በሮችዋን ተመለከትሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሸለቆውም በር ወጣሁ፤ ወደ ዘንዶውም ምንጭና ወደ ጉድፍ መጣያው በር ሄድሁ፤ የፈረሰውንም የኢየሩሳሌምን ቅጥር፥ በእሳትም የተቃጠሉትን በሮችዋን ተመለከትሁ። |
እነርሱም፣ “በሕይወት ተርፈው ከምርኮ ወደ አገራቸው የተመለሱት ሰዎች በታላቅ መከራና ውርደት ላይ ይገኛሉ፤ የኢየሩሳሌም ቅጥር ፈራርሷል፤ በሮቿም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ።
እኔም የይሁዳን መሪዎች በቅጥሩ ግንብ ዐናት ላይ እንዲወጡ አደረግሁ፤ ደግሞም ምስጋና እንዲያቀርቡ ሁለት ታላላቅ የመዘምራን ቡድን መደብሁ። አንዱ በቅጥሩ ግንብ ዐናት በስተቀኝ በኩል ቈሻሻ መጣያ በር ወደሚባለው ሄደ።
ከጥቂት ሰዎች ጋራ በሌሊት ወጣሁ። ለኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ አምላኬ በልቤ ያኖረውን ነገር ለማንም አልነገርሁም፤ ከተቀመጥሁበት እንስሳ በቀር ከእኔ ጋራ ሌሎች እንስሳት አልነበሩም።
ከዚያም፣ “ያለንበትን ችግር ይኸው ታያላችሁ፤ ኢየሩሳሌም ፈርሳለች፤ በሮቿም በእሳት ጋይተዋል፤ አሁንም ኑና የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንደ ገና እንሥራ፤ ከእንግዲህስ መሣለቂያ አንሆንም” አልኋቸው።