ነህምያ 11:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ዘሮች በጠቅላላ 468 ብርቱ ሰዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ልጆች ሁሉ አራት መቶ ስድሳ ስምንት ኃያላን ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከፋሬስ ዘሮች መካከል በጀግንነታቸው ታዋቂዎች የሆኑ 468 ሰዎች በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሆኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ልጆች ሁሉ አራት መቶ ስድሳ ስምንት ጽኑዓን ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ልጆች ሁሉ አራት መቶ ስድሳ ስምንት ጽኑዓን ነበሩ። |
የይሁዳ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤ በሴሎም በኩል፣ የሴሎማውያን ጐሣ፤ በፋሬስ በኩል፣ የፋሬሳውያን ጐሣ፤ በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤