ይህም ሆኖ መንግሥቱን በሙሉ አልነጥቀውም፤ ነገር ግን ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊትና ስለ መረጥኋት ስለ ኢየሩሳሌም ስል ለልጅህ አንድ ነገድ እሰጠዋለሁ።”
ነህምያ 11:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቅድስቲቱ ከተማ ውስጥ የነበሩት የሌዋውያኑ ቍጥር 284 ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቅድስቲቱ ከተማ የነበሩ ሌዋውያን ሁሉ ሁለት መቶ ሰማንያ አራት ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሌዋውያኑም ወገን በአጠቃላይ 284 ሰዎች በቅድስቲቱ በኢየሩሳሌም ከተማ ይኖሩ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቅድስቲቱ ከተማ የነበሩ ሌዋውያን ሁሉ ሁለት መቶ ሰማንያ አራት ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቅድስቲቱ ከተማ የነበሩ ሌዋውያን ሁሉ ሁለት መቶ ሰማንያ አራት ነበሩ። |
ይህም ሆኖ መንግሥቱን በሙሉ አልነጥቀውም፤ ነገር ግን ስለ ባሪያዬ ስለ ዳዊትና ስለ መረጥኋት ስለ ኢየሩሳሌም ስል ለልጅህ አንድ ነገድ እሰጠዋለሁ።”
በዚህ ጊዜ የሕዝቡ መሪዎች መኖሪያቸውን በኢየሩሳሌም አደረጉ፤ ከቀረው ሕዝብ ከዐሥር አንዱ እጅ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፣ የቀሩት ዘጠኙ እጅ ደግሞ በየራሳቸው ከተሞች እንዲኖሩ ዕጣ ተጣጣሉ።
በምስጋናና በጸሎት ጊዜ ይመራ የነበረው የዋናው አለቃ የአሳፍ ልጅ፣ የዘብዲ ልጅ፣ የሚካ ልጅ መታንያ፣ ከወንድሞቹ ሁለተኛ የሆነው በቅቡቅያ፣ የኤዶታም ልጅ፣ የጋላል ልጅ፣ የሳሙስ ልጅ አብድያ።
“ዐመፃን ለማስቆም፣ ኀጢአትን ለማስወገድ፣ በደልን ለማስተስረይ፣ ዘላለማዊ ጽድቅን ለማምጣት፣ ራእይንና ትንቢትን ለማተምና፣ እጅግ ቅዱስ የሆነውን ለመቀባት ስለ ሕዝብህና ስለ ተቀደሰችው ከተማህ ሰባ ሱባዔ ታውጇል።