በሙሴ ሕግ በተጻፈው መሠረት በፍጹም ልቡ፣ በፍጹም ነፍሱ፣ በፍጹም ኀይሉ ወደ እግዚአብሔር የተመለሰ፣ እንደ ኢዮስያስ ያለ ንጉሥ፣ ከርሱ በፊትም ሆነ ከርሱ በኋላ ፈጽሞ አልተነሣም።
ነህምያ 10:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሴት ልጆቻችንን በዙሪያችን ላሉት አሕዛብ አንሰጥም፤ የእነርሱን ሴቶች ልጆች ለወንዶች ልጆቻችን አንወስድም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከወንድሞቻቸውና ከመኳንንቶቻቸው ጋር በመሆን በእግዚአብሔር ባርያ በሙሴ እጅ በተሰጠው በእግዚአብሔር ሕግ ለመሄድ፥ የጌታ አምላካችንን ትእዛዞቹን ሁሉ፥ ፍርዶቹንና ሥርዓቶቹን ለመጠበቅና ለማድረግ ወደ እርግማንና መሐላ ገቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአካባቢአችን ላሉት አሕዛብ ሴቶች ልጆቻችንን በጋብቻ እንደማንሰጥና ወይም የእነርሱን ሴቶች ልጆች ለወንዶች ልጆቻችን በጋብቻ እንደማንወስድ ቃል እንገባለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴቶች ልጆቻችንንም ለምድር አሕዛብ አንሰጥም፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለልጆቻችን አንወስድም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴቶች ልጆቻችንንም ለምድር አሕዛብ አንሰጥም፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለልጆቻችን አንወስድም፥ |
በሙሴ ሕግ በተጻፈው መሠረት በፍጹም ልቡ፣ በፍጹም ነፍሱ፣ በፍጹም ኀይሉ ወደ እግዚአብሔር የተመለሰ፣ እንደ ኢዮስያስ ያለ ንጉሥ፣ ከርሱ በፊትም ሆነ ከርሱ በኋላ ፈጽሞ አልተነሣም።
ንጉሡም በዐምዱ አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ እግዚአብሔርን እንደሚከተል ትእዛዞቹን፣ ደንቦቹን፣ ሥርዐቶቹን በፍጹም ልቡና በፍጹምም ነፍሱ እንደሚጠብቅ፣ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈውን ኪዳን እንደሚያጸና በእግዚአብሔር ፊት ኪዳኑን አደሰ፤ ሕዝቡም ሁሉ ቃል ኪዳን ገቡ።
ንጉሡም በዐምዱ አጠገብ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ እግዚአብሔርን እንደሚከተል ትእዛዞቹን፣ ደንቦቹን፣ ሥርዐቶቹን በፍጹም ልቡና በፍጹምም ነፍሱ እንደሚጠብቅ፣ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈውን ኪዳን እንደሚያጸና በእግዚአብሔር ፊት ኪዳኑን አደሰ።
እኔም ገሠጽኋቸው፤ ርግማንም አወረድሁባቸው። አንዳንዶቹን መታኋቸው፤ ጠጕራቸውንም ነጨሁ። በእግዚአብሔር ስም እንዲህ ስል አማልኋቸው፤ “ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ።
እነርሱም፣ “እንመልሳለን፤ ምንም ዐይነት ትርፍ አንጠይቃቸውም፤ እንዳልኸን እናደርጋለን” አሉ። ካህናቱን ጠራኋቸው፤ መኳንንቱንና ሹማምቱም የገቡትን ቃል እንዲፈጽሙ አማልኋቸው።
ለወንዶች ልጆችህም ሴቶች ልጆቻቸውን ስታጭላቸውና እነዚህም ሴቶች ልጆች አምላኮቻቸውን በመከተል ሲያመነዝሩ፣ ወንዶች ልጆችህን ተመሳሳይ ድርጊት እንዲፈጽሙ ያነሣሧቸዋል።