ናሆም 3:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢትዮጵያና ግብጽ ወሰን የለሽ ኀይሏ ናቸው፤ ፉጥና ሊቢያም ረዳቶቿ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢትዮጵያና ግብጽ ወሰን የለሽ ኃይልዋ ነበሩ፤ ፉጥና ልብያ ረዳቶችዋ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወሰን የሌለው ኀይልዋ ከግብጽ ከራስዋና ከኢትዮጵያ ይመጣ ነበር፤ የፉጥና ሊብያ ሰዎችም ተባባሪዎችዋ ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢትዮጵያና ግብጽ የማይቈጠር ኃይልዋ ነበሩ፣ ፉጥና ልብያ ረዳቶችዋ ነበሩ። |
ከግብጽ ዐብረውት የመጡትን ዐሥራ ሁለት ሺሕ ሠረገላዎች፣ ስድሳ ሺሕ ፈረሰኞችና ስፍር ቍጥር የሌላቸውን የሊቢያ፣ የሱኪምና የኢትዮጵያ ወታደሮችን ይዞ፣
ኢትዮጵያውያንና ሊቢያውያን ብዙ ቍጥር ካላቸው ሠረገላዎቻቸውና ፈረሶቻቸው ጋራ ኀያል ሰራዊት አልነበሩምን? ይሁን እንጂ በእግዚአብሔር ስለ ታመንህ በእጅህ አሳልፎ ሰጠህ፤
ፈረሶች ሆይ ዘልላችሁ ውጡ፤ ሠረገሎችም ሸምጥጡ፤ ጋሻ ያነገባችሁ የኢትዮጵያና የፉጥ ሰዎች፣ ቀስት የገተራችሁ የሉድ ጀግኖች፣ እናንተ ብርቱ ጦረኞች ተነሥታችሁ ዝመቱ።
“ ‘የፋርስ፣ የሉድና የፉጥ ሰዎች፣ ወታደር ሆነው በሰራዊትሽ ውስጥ አገለገሉ፤ ሞገስም ይሆኑሽ ዘንድ፣ ጋሻቸውንና የራስ ቍራቸውን በግድግዳሽ ላይ ሰቀሉ።