“አሁንም አንቺ ቅምጥል ፍጡር፣ በራስሽ ተማምነሽ የምትቀመጪ፣ በልብሽም፣ ‘እኔ ነኝ፣ ከእኔ በቀር ሌላ የለም፤ ከእንግዲህ መበለት አልሆንም፤ የወላድ መካንም አልሆንም’ የምትይ ስሚ!
ናሆም 3:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ሁሉ የሆነው ቅጥ ባጣች፣ አሳሳችና መተተኛ በሆነች ዘማዊት ምክንያት ነው፤ ይህች የጠንቋዮች እመቤት በዝሙቷ አሕዛብን፣ በጥንቈላዋም ሕዝቦችን ባሪያ ያደረገች ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ተዋበችው ጋለሞታ ግልሙትና ብዛት ይህ ሆኖአል፤ እርሷም በመተትዋ እጅግ በለጠች፥ አሕዛብንም በግልሙትናዋ፥ ወገኖችንም በመተትዋ ሸጠች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሆነው ገደብ በሌለው የአምንዝራይቱ ፍትወት ምክንያት ነው፤ እርስዋ በመተት እመቤትነትና በቊንጅናዋ የምታታልልና መንግሥታትን በዝሙትዋ፥ ሕዝቦችን በጥንቈላዋ የምትማርክ ነች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ተዋበችው ጋለሞታ ግልሙትና ብዛት ይህ ሆኖአል፣ እርስዋም በመተትዋ እጅግ በለጠች፥ አሕዛብንም በግልሙትናዋ፥ ወገኖችንም በመተትዋ ሸጠች። |
“አሁንም አንቺ ቅምጥል ፍጡር፣ በራስሽ ተማምነሽ የምትቀመጪ፣ በልብሽም፣ ‘እኔ ነኝ፣ ከእኔ በቀር ሌላ የለም፤ ከእንግዲህ መበለት አልሆንም፤ የወላድ መካንም አልሆንም’ የምትይ ስሚ!
እነዚህ ሁለት ነገሮች፣ መበለትነትና የወላድ መካንነት፣ አንድ ቀን ድንገት ይመጡብሻል፤ የቱን ያህል አስማት፣ የቱንም ያህል መተት ቢኖርሽ፣ በሙሉ ኀይላቸው ይመጡብሻል።
የመብራት ብርሃን፣ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይበራም፤ የሙሽራውና የሙሽራዪቱ ድምፅ፣ ዳግመኛ በአንቺ ውስጥ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የዓለም ታላላቅ ሰዎች ነበሩ፤ በአስማትሽም ሕዝቦች ሁሉ ስተዋል።