ሚልክያስ 2:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከርሱ ጋራ የገባሁት ኪዳን የሕይወትና የሰላም ኪዳን ነበር፤ እነርሱንም ሰጠሁት፤ ይህም ክብርን አመጣ፤ እርሱም አከበረኝ፤ ስሜን በመፍራትም ጸና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃል ኪዳኔ ከእርሱ ጋር የሕይወትና የሰላም ነበረ፤ እንዲያከብረኝ እነርሱን ሰጠሁት፤ እርሱም አከበረኝ፥ ከስሜም በማክበር ፈራኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሰጠኋቸው ቃል ኪዳን የሕይወትና የሰላም ቃል ኪዳን ነው፤ እንዲሁም እኔን የማክበር ግዴታ አለባቸው፤ እነርሱም እኔን እየፈሩ ስሜን አክብረው ኖረዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃል ኪዳኔ ከእርሱ ጋር የሕይወትና የሰላም ቃል ኪዳን ነበረ፣ ይፈራ ዘንድም እነርሱን ሰጠሁት፣ እርሱም ፈራኝ፥ ከስሜም የተነሣ ደነገጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃል ኪዳኔ ከእርሱ ጋር የሕይወትና የሰላም ቃል ኪዳን ነበረ፥ ይፈራ ዘንድም እነርሱን ሰጠሁት፥ እርሱም ፈራኝ፥ ከስሜም የተነሣ ደነገጠ። |
“ ‘ከእነርሱ ጋራ የሰላም ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ከዚያም ምድሪቱን ከዱር አራዊት ነጻ አደርጋለሁ፤ እነርሱም በምድረ በዳ ይኖራሉ፤ በደንም ውስጥ ያለ ሥጋት ይተኛሉ።
ከእነርሱም ጋራ የሰላም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ቃል ኪዳኑም የዘላለም ይሆናል። አጸናቸዋለሁ፤ አበዛቸዋለሁ፤ መቅደሴንም በመካከላቸው ለዘላለም አኖራለሁ።
እስራኤላዊውን ተከትሎ ወደ ድንኳኑ ገባ፤ ጦሩንም ወርውሮ እስራኤላዊውንና ሴቲቱን አጣምሮ ወጋቸው። ከዚያም በእስራኤላውያን ላይ የወረደው መቅሠፍት ተከለከለ፤
“በእስራኤላውያን በኵሮች ምትክ ሌዋውያኑን፣ በከብቶቻቸውም ምትክ የሌዋውያኑን ከብቶች ውሰድ፤ ሌዋውያኑም የእኔ ይሁኑ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።