ከኅብረት መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ ቍርባን አድርጎ ያምጣ፤ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፣ በሆድ ዕቃው ላይ ያለውን ሥብ ሁሉ፣
ዘሌዋውያን 4:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለኅብረት መሥዋዕት ከሚቀርበው ወይፈን እንዳወጣ ሁሉ ሥቡን ያውጣ፤ ካህኑም የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ያቃጥለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለአንድነት መሥዋዕት ከሚቀርበው ወይፈን እንደሚወሰደው ከወሰደ በኋላ፥ ካህኑ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ያቃጥለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሊቀ ካህናቱም ይህን ስብ ሁሉ ተቀብሎ የሚቃጠል መሥዋዕት በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ያቃጥለው፤ አፈጻጸሙም ለአንድነት መሥዋዕት ከሚቀርበው የእንስሳ ስብ ወስዶ ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚያቀርበው ዐይነት ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለደኅንነት መሥዋዕት ከታረደው ወይፈን እንደ ተወሰደው ይወስዳል፤ ካህኑም ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ያቀርበዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለደኅንነት መሥዋዕት ከታረደው ወይፈን እንደ ተወሰደው ይወስዳል። ካህኑም ለሚቃጠል መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ያቃጥለዋል። |
ከኅብረት መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ ቍርባን አድርጎ ያምጣ፤ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሥብ፣ በሆድ ዕቃው ላይ ያለውን ሥብ ሁሉ፣