ዘሌዋውያን 24:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናቱ እስራኤላዊት፣ አባቱ ግብጻዊ የሆነ አንድ ሰው በእስራኤላውያን መካከል ወጣ፤ በሰፈርም ውስጥ ከአንድ እስራኤላዊ ጋራ ተጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቱ ግብፃዊ የነበረ የእስራኤላዊት ልጅ በእስራኤል ልጆች መካከል ወጣ፤ የእስራኤላዊቱ ልጅና አንድ እስራኤላዊ በሰፈር ውስጥ ተጣሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናቱ እስራኤላዊት፥ አባቱ ግብጻዊ የሆነ አንድ ሰው በእስራኤላውያን መካከል ወጥቶ ከአንድ እስራኤላዊ ጋር ተጣላ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቱ ግብፃዊ የነበረ የእስራኤላዊት ሴት ልጅ በእስራኤል ልጆች መካከል ወጣ፤ የእስራኤላዊቱ ሴት ልጅና አንድ እስራኤላዊ ሰው በሰፈር ውስጥ ተጣሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቱ ግብፃዊ የነበረ የእስራኤላዊት ልጅ በእስራኤል ልጆች መካከል ወጣ፤ የእስራኤላዊቱ ልጅና አንድ እስራኤላዊ በሰፈር ተጣሉ፤ |
የእስራኤላዊቱ ልጅ የእግዚአብሔርን ስም በማቃለል ሰደበ፤ ስለዚህም ወደ ሙሴ አመጡት፤ የሰውየው እናት ስም ሰሎሚት ነበር፤ እርሷም ከዳን ወገን የተወለደው የደብራይ ልጅ ነበረች።
ኅብስቱ የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ነው፤ በተቀደሰ ስፍራም ይበሉታል፤ ለእግዚአብሔር በእሳት ከሚቀርበው መሥዋዕት እጅግ የተቀደሰ ድርሻቸው ነውና።”