La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 17:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ እስራኤላውያንን፣ “ከእናንተ ማንም ደም አይብላ፤ በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛም ቢሆን ደም አይብላ” አልሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ አልሁ፦ ከእናንተ ማንም ሰው ደምን አይብላ፥ በመካከላችሁም ከሚኖር እንግዳ ማንም ሰው ደምን አይብላ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ለእስራኤላውያን የምለው ይህ ነው፤ ከእናንተ ማንም፥ ወይም በመካከላችሁ ከሚኖሩ ማንኛውም መጻተኛ ደም መብላት የለበትም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች፦ ‘ከእ​ና​ንተ ማንም ደምን አይ​በ​ላም፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ች​ሁም ከሚ​ኖሩ እን​ግ​ዶች ማንም ደምን አይ​በ​ላም’ አልሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለዚህ የእስራኤልን ልጆች፦ ከእናንተ ማንም ደምን አይበላም፥ በመካከላችሁም ከሚኖሩ እንግዶች ማንም ደምን አይበላም አልሁ።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 17:12
5 Referencias Cruzadas  

ይህም ሕግ በዜጋውም ሆነ በመካከላችሁ በሚኖሩት መጻተኞች ላይ እኩል ተፈጻሚነት ይኖረዋል።”


ስለዚህ እንዲህ በላቸው፣ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሥጋውን ከነደሙ ትበላላችሁ፤ ዐይኖቻችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፤ ደምም ታፈስሳላችሁ፤ ታዲያ በዚህ ሁኔታ ምድሪቱን ልትወርሱ ታስባላችሁ?


የፍጡር ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ በመሠዊያ ላይ ለሕይወታችሁ ማስተስረያ እንዲሆን ደሙን ሰጥቻችኋለሁ፤ ለሰውም ሕይወት ስርየት የሚያስገኝ ደም ነው።


“ ‘እንዲበላ የተፈቀደውን ማንኛውንም እንስሳ ወይም ወፍ ዐድኖ የያዘ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላችሁ የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ደሙን ከውስጡ ያፍስስ፤ ዐፈርም ያልብሰው፤


“ ‘በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ፣ ሥብ ወይም ደም ከቶ አትብሉ፤ ይህ ለመጪው ትውልድ ሁሉ የተሰጠ የዘላለም ሥርዐት ነው።’ ”