ዘሌዋውያን 13:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አንድ ሰው በገላው ላይ ዕባጭ ወጥቶ ቢድን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰውነቱም ቆዳ ላይ የዳነ የብጉንጅ ቁስል ቢኖር፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አንድ ሰው የዳነ እባጭ ቢኖርበትና፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በሥጋውም ቆዳ ላይ ቍስል ቢሆንና ቢሽር፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሥጋውም ቁርበት ላይ ቍስል ቢሆንና ቢሽር፥ |
እርሱም አለ፤ “የአምላካችሁን እግዚአብሔር ድምፅ በጥንቃቄ ብትሰሙ፣ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብትፈጽሙ፣ ትእዛዞቹን ልብ ብትሉና ሥርዐቱንም ሁሉ ብትጠብቁ፣ በግብጻውያን ላይ ያመጣሁባቸውን ማንኛውንም ዐይነት በሽታ በእናንተ ላይ አላመጣም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝና።”
ካህኑ ይመርምረው፤ ቋቍቻው ባለበትም ቦታ ያለው ጠጕር ቢነጣና ከቈዳው በታች ዘልቆ ቢገባ፣ በቃጠሎው ሰበብ ከውስጥ የወጣ ተላላፊ በሽታ ነው፤ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ፤ ተላላፊ የቈዳ በሽታ ነው።