ዘሌዋውያን 11:41 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ምድር ለምድር የሚንቀሳቀስ ማንኛውም ፍጡር ጸያፍ ነው፤ አይበላም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በምድርም ላይ የሚርመሰመስ ተንቀሳቃሽ ሁሉ ጸያፍ ነው፥ አይበላም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በምድር ላይ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ትናንሽ ነፍሳት ሁሉ የማይበሉና በእናንተ ዘንድ የተጠሉ ይሁኑ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በምድርም ላይ የሚንቀሳቀስ ተንቀሳቃሽ አውሬ ሁሉ ለእናንተ ርኩስ ነው፤ አትብሉትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድርም ላይ የሚንቀሳቀስ ተንቀሳቃሽ ሁሉ የተጸየፈ ነው፥ አትብሉትም። |
ምድር ለምድር የሚንቀሳቀሰውን ፍጡር ሁሉ፣ ይኸውም በደረቱ የሚሳበውን ወይም በአራት እግር የሚሄደውን ወይም ብዙ እግሮች ያሉትን አትብሉ፤ ጸያፍ ነው።