ሰቈቃወ 3:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርዳታ ፈልጌ ብጣራና ብጮኽ እንኳ፣ ጸሎቴን መስማት አልፈለገም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጠራሁና በጮኽሁ ጊዜ ጸሎቴ ከለከለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእርዳታ ጩኸቴን ባሰማም እንኳ አላዳምጥ አለኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጠራሁና በጮኽሁ ጊዜ ጸሎቴ ተከለከለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጠራሁና በጮኽሁ ጊዜ ጸሎቴ ከለከለ። |
በዘጠኝ ሰዓት ገደማ፣ ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ፣ “ኤሎሄ! ኤሎሄ! ላማ ሰበቅታኒ?” እያለ ጮኸ፤ ትርጕሙም “አምላኬ፤ አምላኬ፤ ለምን ተውኸኝ?” ማለት ነው።