ዮሐንስ 4:37 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ፣ ‘አንዱ ይዘራል፤ ሌላውም ያጭዳል’ የተባለው ምሳሌ እውነት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ‘አንዱ ይዘራል፤ አንዱም ያጭዳል፤’ የሚለው ቃል በዚህ እውነት ሆኖአልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ምክንያት ‘አንዱ ይዘራል፥ ሌላው ያጭዳል’ የተባለው አባባል እውነት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንዱ ይዘራል፥ ሌላውም ያጭዳል የሚለው ቃል በዚህ እውነት ሆኖአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንዱ ይዘራል አንዱም ያጭዳል የሚለው ቃል በዚህ እውነት ሆኖአልና። |
ትዘራለህ፤ ነገር ግን አታጭድም፤ የወይራ ዘይት ትጨምቃለህ፤ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፤ ወይንን ትቈርጣለህ፤ ነገር ግን የወይን ጠጅ አትጠጣም።
ዐጫጁ አሁንም ቢሆን እንኳ ደመወዙን እየተቀበለ ነው፤ ለዘላለም ሕይወት ይሆን ዘንድ አዝመራውን ይሰበስባል፤ ይህም ዘሪውና ዐጫጁ በጋራ ደስ እንዲላቸው ነው።