ይሥሐቅም አባቱን አብርሃምን፣ “አባቴ ሆይ” አለው። አብርሃምም፣ “እነሆኝ፤ አለሁ ልጄ” አለው። ይሥሐቅም፣ “እሳቱና ዕንጨቱ ይኸው፤ ነገር ግን የሚቃጠለው መሥዋዕት በግ የት አለ?” ብሎ ጠየቀ።
ዮሐንስ 1:36 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስንም በዚያ ሲያልፍ አይቶ፣ “እነሆ፤ የእግዚአብሔር በግ!” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስንም ሲራመድ ተመልክቶ “እነሆ የእግዚአብሔር በግ፤” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሐንስ ኢየሱስን በዚያ ሲያልፍ አይቶ፥ “እነሆ፥ የእግዚአብሔር በግ!” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስን ሲሄድ አይቶ “እነሆ፥ የዓለሙን ኀጢኣት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ሲሄድ ተመልክቶ፦ እነሆ የእግዚአብሔር በግ አለ። |
ይሥሐቅም አባቱን አብርሃምን፣ “አባቴ ሆይ” አለው። አብርሃምም፣ “እነሆኝ፤ አለሁ ልጄ” አለው። ይሥሐቅም፣ “እሳቱና ዕንጨቱ ይኸው፤ ነገር ግን የሚቃጠለው መሥዋዕት በግ የት አለ?” ብሎ ጠየቀ።
የእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፣ የመስቀሉንም ውርደት ንቆ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል።