በኢየሩሳሌም ተቀምጦ እንዳይገዛም ፈርዖን ኒካዑ በሐማት ምድር ሪብላ በምትባል ቦታ አሰረው፤ በአገሩም ላይ አንድ መቶ መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ግብር ጣለበት።
ኤርምያስ 52:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክብር ዘበኞቹ አዛዥ ናቡዘረዳን እነዚህን ሁሉ ይዞ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ነበረበት ወደ ሪብላ አመጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ወስዶ የባቢሎን ንጉሥ ወዳለበት ወደ ሪብላ አመጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ናቡዛርዳን እነዚህን ሁሉ በሐማት ግዛት ውስጥ በሪብላ ከተማ ወደነበረው ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወሰዳቸው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአዛዦቹም አለቃ ናቡዛርዳን ወስዶ የባቢሎን ንጉሥ ወዳለበት ወደ ዴብላታ ወሰዳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዘበኞቹም አለቃ ናቡዘረዳን ወስዶ የባቢሎን ንጉሥ ወዳለበት ወደ ሪብላ አመጣቸው። |
በኢየሩሳሌም ተቀምጦ እንዳይገዛም ፈርዖን ኒካዑ በሐማት ምድር ሪብላ በምትባል ቦታ አሰረው፤ በአገሩም ላይ አንድ መቶ መክሊት ብርና አንድ መክሊት ወርቅ ግብር ጣለበት።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በነገሠ በዐሥራ ዘጠነኛው ዓመት፣ በዐምስተኛው ወር ከወሩም በሰባተኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ባለሟል የክብር ዘበኞች አዛዥ የነበረው ናቡዘረዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።
ይሁን እንጂ የባቢሎናውያንም ሰራዊት ግን ተከትሎ አሳደዳቸው፣ በኢያሪኮም ሜዳ ደርሶባቸው ሴዴቅያስን ያዘ፤ ማርከውም በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ሪብላ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር አመጡት፤ በዚያም የባቢሎን ንጉሥ ፈረደበት።
ወሰኑም ከሴፋማ አንሥቶ ከዓይን በስተምሥራቅ እስካለው እስከ ሪብላ ቍልቍል ይወርድና ከኪኔሬት ባሕር በስተምሥራቅ እስካሉት ሸንተረሮች ድረስ ይዘልቃል።