ኤርምያስ 52:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንዱ ዐምድ ዐናት ላይ ያለው የናስ ጕልላት ቁመት ዐምስት ክንድ ሲሆን፣ ዙሪያውንም ሁሉ የሮማን ቅርጽ ባላቸው የናስ ጌጣጌጦች የተዋበ ነበር፤ ሌላውም ዐምድ የሮማኑን ጌጣጌጥ ጨምሮ ከዚሁ ጋራ ተመሳሳይ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የናሱም ጉልላት በላዩ ነበረ፤ የአንዱም ጉልላት ቁመት አምስት ክንድ ነበረ፥ በጉልላቱም ላይ በዙሪያው ሁሉ ከናስ የተሠሩ መረበብና ሮማኖች ነበሩበት፤ በሁለተኛውም ዓምድ ደግሞ እንደዚህ ያለ ነገርና ሮማኖች ነበሩበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእያንዳንዱም ምሰሶ ጒልላት ከነሐስ የተሠራ ሆኖ ሁለት ሜትር ያኽል ከፍታ የነበረውና በመረብና በሮማን ፍሬ ቅርጽ የተጌጠ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የናሱም ጕልላት በላዩ ነበረ፤ የአንዱም ጕልላት ቁመት አምስት ክንድ ነበረ፤ በጕልላቱም ላይ በዙሪያው ሁሉ ከናስ የተሠሩ መርበብና ሮማኖች ነበሩበት፤ በሁለተኛውም ዐምድ ደግሞ እንደዚህ ያለ ነገርና ሮማኖች ነበሩበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የናሱም ጕልላት በላዩ ነበረ፥ የአንዱም ጉልላት ቁመት አምስት ክንድ ነበረ፥ በጕልላቱም ላይ በዙሪያው ሁሉ ከናስ የተሠሩ መረበብና ሮማኖች ነበሩበት፥ በሁለተኛውም ዓምድ ደግሞ እንደዚህ ያለ ነገርና ሮማኖች ነበሩበት። |
እያንዳንዱም ዐምድ ከፍታው ዐሥራ ስምንት ክንድ ሲሆን፣ የናስ ጕልላት ነበረው፤ የጕልላቱ ርዝመት ሦስት ክንድ ሆኖ፣ ዙሪያውን በሙሉ የናስ መርበብና የሮማን ፍሬዎች ቅርጽ ነበረው፤ ሌላውም ዐምድ ከነቅርጾቹ ከዚሁ ጋራ ተመሳሳይ ነበር።
በቤተ መቅደሱም ፊት ለፊት በአንድነት ቁመቱ ሠላሳ ዐምስት ክንድ የሆነ፣ በእያንዳንዱም ላይ ዐምስት ክንድ ጕልላት ያለው ሁለት ዐምድ ሠራ።