ኤርምያስ 51:43 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተሞቿ ሰው የማይኖርባቸው፣ ዝርም የማይልባቸው፣ ደረቅና ምድረ በዳ፣ ባድማ ምድርም ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር ምድረ በዳም፥ ሰውም የማይቀመጥባቸው የሰውም ልጅ የማያልፍባቸው ምድር ሆኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከተሞቹ ውሃ የማይገኝባቸውና ማንም ሊኖርባቸውም ሆነ ሊተላለፍባቸው የማይችል ምድረ በዳ ሆነዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር፥ ሰውም የማይቀመጥበት፥ የሰውም ልጅ የማያልፍበት ምድር ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተሞችዋ ባድማና ደረቅ ምድር ምድረ በዳም፥ ሰውም የማይቀመጥበት የሰውም ልጅ የማያልፍበት ምድር ሆኑ። |
ጥፋት ይመጣብሻል፤ ነገር ግን በአስማትሽ እንዴት እንደምታርቂው አታውቂም፤ ወጆ ከፍለሽ ለማስወገድ የማትችዪው፣ ጕዳት ይወድቅብሻል፤ ያላሰብሽው አደጋ፣ ድንገት ይደርስብሻል።
እነርሱም፣ ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን፣ በወና ምድረ በዳ፣ በጐድጓዳና በበረሓ መሬት፣ በደረቅና በጨለማ ቦታ፣ ሰው በማያልፍበትና በማይኖርበት ስፍራ የመራን እግዚአብሔር ወዴት ነው?’ ብለው አልጠየቁም።
ሰው በዚያ መኖር እስከማይችል ድረስ፣ የባቢሎንን ምድር ባድማ ለማድረግ፣ እግዚአብሔር በባቢሎን ላይ ያቀደው ስለሚጸና፣ ምድር ትናወጣለች፤ በሥቃይም ትወራጫለች።